ሚያዝያ 18 2017 - በአዲስ አበባ በጠንካራ የቁጥጥር ስራ የመሬት ወረራን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል ተባለ።
- sheger1021fm
- Apr 26
- 1 min read
በአዲስ አበባ በጠንካራ የቁጥጥር ስራ የመሬት ወረራን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል ተባለ።
የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው።
በተቋማቱ ጠንካራ የቁጥጥር ስራ በከተማዋ በስፋት ይታይ የነበረው የመሬት ወረራ መቀነሱን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የግምገማ መድረኩን ሲከፍቱ ተናግረዋል።
በዘጠኝ ወራቱ በከተማዋ የተፈፀመ የመሬት ወረራ የለም ነው የተባለው።

በዘጠኝ ወራቱ 33,000 ተጨማሪ የሠላም ሠራዊት አባላት ተመልምለው እና ሠልጥነው ነባሮቹን እንደተቀላቀሉም ወይዘሮ ሊዲያ ጠቅሰዋል።
በከተማዋ የሚካሄደውን የኮሪደር ልማት ተከትሎ የደህንነት ካሜራዎችን እና መብራቶችን በሚገባው መጠን ማሟላት ላይ ግን አሁንም የሚቀሩ ስራዎች አሉ ብለዋል።
በአዲስ አበባ ባህልና ትያትር አዳራሽ እየተካሄደ ባለው በዚህ ውይይት ከከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የደንብ ማስከበር ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments