top of page

ሚያዝያ  18፣2016 - በአዲስ መልክ የቋቋመው ‘’የንግድ ስራ አመራር ማሰልጠኛ አካዳሚ’’ ተመርቋል

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የንግዱ ማህበረሰብ የተሻለ አቅም ፈጥሮ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን በስልጠና መደገፌን እቀጥላለሁ አለ፡፡

 

ምክር ቤቱ በአዲስ መልክ ያቋቋመውን ‘’የንግድ ስራ አመራር ማሰልጠኛ አካዳሚ’’ አስመርቋል።

                       

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በንግድ ስራ ዙሪያ ተቋም አደራጅቶ ስልጠና መስጠት የጀመረው ከአስር አመት በፊት እንደሆነ ይናገራል።

 


ጥናት ላይ ተመስርቶ በተደራጀው እና ስልጠና ሲሰጥበት በቆየው በዚህ ተቋም ብዙዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን፤

የምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ አቶ ውቤ መንግስቱ አውስተዋል።

 

ምክር ቤቱ ለአስር አመት ሲያሰለጥን የቆየበትን ተቋም ‘’የንግድ ስራ አመራር ማሰልጠኛ ተቋም’’ በሚል በአዲስ መልክ እንዳደራጀው ዋና ፀሃፊው ተናግረዋል።

 

በተቋሙ የሚሰጡ መርሃ ግብሮች እና ብቁ የሆኑ ባለሞያዎች መለየታቸውንም አቶ ውቤ ተናግረዋል።

 

ተቋሙን በመጠቀም የንግዱ ማህበረሰብ የተሻለ አቅም ፈጥሮ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን በስልጠና መደገፋችንን እንቀጥላለንም ብለዋል ዋና ፀሃፊው።

 

የንግድ ስራዎችን የሚመሩ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች በዚህ ተቋም የስልጠና ዕድል ከሚያገኙት መካከል እንደሚሆኑ ሠምተናል።

 

ከቴክኖሎጂ ጋር የተቆራኘ ስራ መስራትን የሚያስተምር ተቋም ይሆናል ሲሉም አቶ ውቤ ተናግረዋል።

 

 መደበኛ የሆነው የንግድ ስራ አመራር ስልጠና እንዲሁ በተቋሙ ይሰጣል ተብሏል።

 

ንጋቱ ረጋሳ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

Telegram:  @ShegerFMRadio102_1

 

 

 

bottom of page