ሚያዝያ 17 2017 - ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችን ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
- sheger1021fm
- Apr 25
- 1 min read
ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ ወጪ፤ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችን ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡
በቢልና ሚሊናዳ ጌትስ ፋውንዴስን በተገኘ የ14.3 ሚሊዮን ዶላር ወይም በወቅቱ የምንዛሪ ተመን ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጤና ሚኒስቴርና በኤምኤስአይ #MSI ኢትዮጵያ የሚተገበር ነው፡፡
ለ4 ዓመታት ይተገባራል በተባለው ፕሮጀክቱ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በሲዳማ ክልሎች አማራጭ የጤና አገልግሎት፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚሰጥበት መሆኑን በMSI ሪፕሮዳክቲቭ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አበበ ሽብሩ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡

በፕሮጀክቱ በእነዚህ አራቱ ክልሎች ውስጥ ባሉ 230 የመንግስት የጤና ተቋማት አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የነገሩን ዶክተር አበበ በአንድ በኩል የጤና ባለሞያዎቹን አቅም በማጎልበት፤ በሌላ በኩል ምንም አይነት የጤና አገልግሎት በሌለባቸው ቦታዎች በ6 ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድኖች የተጠቀሱትን የጤና አገልግሎቶች እንደሚሰጡም አስረድተዋል፡፡
ስራው የሚከወንባቸው 4ቱ ክልሎች የተመረጡት በግጭቶች ምክንያት እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በተለይ እናቶች እና ህፃናት በይበልጥ ተጎጂ እንደመሆናቸው ለእነርሱ አማራጭ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ነው ብለውናል ዶክተር አበበ፡፡
ስራውን በበላይነት የሚመራው የጤና ሚኒስቴር ሆኖ MSI ኢትዮጵያ ስራውን በማገዝ ድርሻውን ይወጣል ተብሏል፡፡
ለስራው የተመደበውን የ1.7 ቢሊዮን ብር በቢልጌትስ ፋውንዴሽን እንዲሸፈን ያደረገው MSI ኢትዮጵያ መሆኑን ከሃላፊው ሰምተናል፡፡
የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆነና በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘ 520 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ MSI ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል የስነ ተዋልዶ ጤና ፕሮጀክት በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/fbgdfdfbh/
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r












Comments