top of page

ሚያዝያ 16፣2016በአዲስ አበባ በአፈር እና ግንብ መናድ አደጋ ስድስት ሰዎች ሞቱ፡፡

በአዲስ አበባ በአፈር እና ግንብ መናድ አደጋ ስድስት ሰዎች ሞቱ፡፡


አደጋው ያጋጠመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጅድ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ሌሊት 11:00 ሰዓት ላይ ነው ተብሏል፡፡

የግለሰብ መኖሪያ ቤት አፈርና ግንብ ተንዶ በደረሰው በዚህ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው የነበሩ ናቸው ተብሏል።


በአደጋው ምክንያት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የደረሰውን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ወደፊት እናሳውቃለን ሲሉ የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።


ንጋቱ ረጋሳ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1




bottom of page