ሚያዝያ 15 2017 - የሚያመርቱትን የስንዴ ዱቄትና ዘይት በተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲያበለፅጉ በህግ ቢገደዱም ይህን ያላደረጉ 26 አምራቾች መታገዳቸው ተሰማ
- sheger1021fm
- Apr 23
- 1 min read
የሚያመርቱትን የስንዴ ዱቄትና ዘይት በተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲያበለፅጉ በህግ ቢገደዱም ይህን ያላደረጉ 26 አምራቾች መታገዳቸው ተሰማ፡፡
ለ65 የስንዴ ዱቄትና ዘይት አምራቾች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡
ይህን ያለው የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን ነው፡፡
ከዚህ ቀደም ባለስልጣን መ/ቤቱ የስንዴ ዱቄትና ዘይትን በቫይታሚንና በሌሎች ንጥረ ነገሮች አንዲበለጽጉ አስገዳጅ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም 65 የሚሆኑ አምራቾችን ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውና ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 26ቱን መታገዳቸወን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡
ይህ አይነቱ ክትትል እና እገዳ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ የተደረገ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ለእነዚህ አምራቾች የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቷቸው የቆየ መሆኑንና የእፎይታ ጊዜ ማብቃቱን በመናገር እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ነግሮናል፡፡
እርምጃው በአንድ ጊዜ የተወሰደ እንዳልሆነ የነገሩን በኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን የምግብ ኢንስፔክሽን እና የህግ ማስፈፀሚያ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ ናቸው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r












Comments