መጋቢት 6፣2016 - አየር መንገዱ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር ለነበረው ምስል ምላሽ ሰጠ
- sheger1021fm
- Mar 15, 2024
- 1 min read
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ የአየር መንገዱን ዩኒፎርም የለበሰ ሰራተኛን የራሱን ሻንጣ በማስተካከል ላይ ሳለ የሚያሳይ ምስል ከተሳሳተ መረጃ ጋር በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በመዘዋወር ላይ እንዳለ ተመልክቻለሁ ብሏል።
በማህበራዊ ሚዲያ በተዘዋወረው ምስል ላይ የሚታየው ግለሰብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ባልደረባ ሲሆን የአየር መንገዱ ዓርማ የታተመበት ሻንጣም የሰራተኛው መሆኑን አየር መንገዱ አስረድቷል።
እንዲሁም በምስሉ ላይ የሚታየው ቦታ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ባልደረቦቻችን የግል ንብረቶቻቸውን እና ለስራ የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች የሚያስተካክሉበት አካባቢ መሆኑን እና ሌሎቹ ቦርሳዎችም በምስሉ ላይ ያልተካተቱ የሌሎች ባልደረቦቻችን ቦርሳዎች እንደሆኑ ጠቅሷል።
በተጨማሪም ስፍራው የመንገደኞች ሻንጣ ሊገኝበት የማይችል ለሰራተኞቻችን ብቻ የተከለለ ቦታ ከመሆኑም በተጨማሪም ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት በደህንነት የካሜራ ዕይታ ውስጥ የሚገኝ ነው ብሏል።
በስራ ገበታው ላይ የሚገኝ የአየር መንገዱ ሰራተኛን ተግባር ህገወጥ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ እንዳሳዘነውም በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments