top of page

የቤት ገዢዎችን የመግዛት አቅም ለማበርታት እንዲያግዝ ፖሊሲ የተዘጋጀለት የሞርጌጅ ባንክ እንዲቋቋም ተጠየቀ።

  • 4 days ago
  • 2 min read

ሚያዝያ 20/2018

 

 

የቤት ገዢዎችን የመግዛት አቅም ለማበርታት እንዲያግዝ ፖሊሲ የተዘጋጀለት የሞርጌጅ ባንክ እንዲቋቋም ተጠየቀ።

 

 

በኢትዮጵያ ያለው የግለሰቦች ቤት የመግዛት አቅም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መምጣት፣የብርየመግዛት አቅም መዳከም የግለሰቦች ቤት የመግዛት አቅም አብሮ ተዳክሟል ይላሉ የሪል እስቴት አልሚዎች።

 

 

የኢትዮጵያ የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የቦርድ አባላት እንደነገሩን የቤቶች ግንባታ በውጭ ምንዛሪ ላይ መሰረት ያደገ ነው፣ 55 በመቶ የግንባታ ግብዓቶች ተገዝተው የሚመጡት በውጭ ምንዛሪ ነው ብለውናል፡፡

 

 

በተዘዋዋሪ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውሉት ግብዓቶች ሲጨመሩ የቤት ግንባታ ዘርፉ እስከ 75 በመቶ ወጪው የውጭ ምንዛሪ ላይ የተንጠለጠለ ነው፤ ለዚህ ነው የዶላር ዋጋ ሲጨምርየቤት ዋጋም የሚጨምረው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

 

 

በሪል እስቴት አልሚዎች የሚገነቡ ቤቶች አብዛኛው ማህበረሰብ ማለትም ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ሊገዙት አይደለም ሊያስቡት የሚከብድ ዋጋ የሚጠራባቸው ናቸው ይባላል፡፡

 

 

የሪል እስቴት ገበያው ጥቂት ሰዎችን ብቻ የሚያሳትፍ የመሆኑ ነገር እንዲያበቃ፣ለየትኛውም የቤት ገዢ የረጅም ጊዜ ክፍያን ከአነስተኛ ወለድ ጋር አጣምረው የያዙ የብድር አገልግሎቶችን የሚሰጡ የሞርጌጅ ባንኮች ያስፈልጋሉ የሚሉት የማህበሩ የቦርድ አባላት፣ከዚህ ቀደም የሞርጌች ባንኮች እንዲቋቋሙ ፖሊሲ ተዘጋጅቷል ወደ ተግባር መግባት አለበት የሚል ሃሳብም ያነሳሉ።

 

 

ሌላውና በቤት ገዢዎችና በሪል እስቴት አልሚዎች መካከል ያለው አከራካሪው ጉዳይ የመተማመን ችግር ነው።

 

 

ችግሩ መኖሩን የሚያምኑት አልሚዎቹ ለዚህ ዋንኛው መንስኤ በገዢው በኩል በአነስተኛ ዋጋ ጥሩ በሚሉት አካባቢ የቤት ባለቤት የመሆን ምኞት እንደሆነ ያነሳሉ፣ገዢዎች የተመኙትን

ለማግኘት የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ሳያጣሩ፤የተባለው ቅናሽ እውነተኛ ነው? ለምንስ የተጋነነ ቅናሽ ኖረው?የሚሉ ጉዳዮችን ሳያጣሩ የሚገቡበት ነው ይላሉ፡፡

 

 

በአልሚው በኩል ደግሞ ገዢዎችን በተለያዩ መንገዶች በማታለል የማይፈፀም ቃል እየገቡ በተለይ በጣም የተጋነኑ ማስታወቂያዎችን በማስነገር አሳምኖ ገንዘብ በመሰብሰብ መሰወርእንደሆነም ነግረውናል።

 

 

ስለዚህም በአጭበርባሪዎች እጅ ላይ ላለመውደቅ ''በመሃል ከተማ በማይታመን ዋጋ ''የሚሉ አይነት ማስታወቂያዎችን በጥርጣሬ አይን ማየት ይበጃል ሲሉም ይመክራሉ።

 

 

የኢትዮጵያ የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር በዘርፉ በሁለቱም ወገን የሚፈጠሩ እንዲህ አይነት አለመግባባቶች በግልግል ዳኝነት እየተፈቱ ነው ተብሏል፡፡

 

 

ገዢዎችን ከመጭበርበር ለመጠበቅ የግዢ ውሎችን ሲፈፅሙ ከህግ አማካሪ ጋር እንዲሆን፤በአነስተኛ ዋጋ ጥሩ ቤት ለማግኘት የሚኖር ከመጠን ያለፈ መጓጓት፤ ሳያረጋግጡ እንዲሁ በማመን ገንዘብን መክፈል ለመጭበርበር ያጋልጣል የሚሉ አይነት መልዕክቶችን በማስተላለፍ ገዢው ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ማህበሩ እየሰራ ነው መበሉን ሰምተናል፡፡

 

 

ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page