የናፍታ ነዳጅ አቅርቦት መጠን ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግስት መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ተናገሩ።
- 11 minutes ago
- 1 min read
ሚያዝያ 21/2018
የናፍታ ነዳጅ አቅርቦት መጠን ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግስት መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ፥ በአሁኑ ወቅት ያለውን የምርትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በማየት የናፍታ አቅርቦት ወደነበረበት እንዲመለስ መንግሥት ወስኗል ብለዋል።
በማደያዎች ይቀርብ የነበረው የናፍታ አቅርቦት በቀን በግማሽ ቀንሶ እንደነበር ይታወሳል።
በዚህም መሰረት በቀን ይቀርብ የነበረው ናፍታ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር እንዲሆን ተወስኖ ነበር።
አሁን ላይ ግን ከጦርነቱ በፊት ይቀርብ የነበረው በቀን 9 ሚሊየን ሊትር ናፍታ እንዲገባ መንግስት ወስኗል ብለዋል።
ለዚህም መንግሥት ተጨማሪ 20 ቢሊየን ብር በወር ለነዳጅ ድጎማ እንደሚያደርግ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።
ናፍታው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ ጀምሯል ያሉት ሚኒስትሩ፥አጠቃላይ የነዳጅ ድጎማው ከ300 ቢሊየን ብር መብለጡን ጠቁመዋል።
ቤንዚን እና የአውሮላን ነዳጅም ከጦርነቱ በፊት በነበረው መጠን እየቀረበ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ለአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ ለክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ ከጅቡቲ ናፍታ የማጓጓዝ ሥራ እንደሚከናወን ሚኒስትሩ መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

