top of page

መጋቢት 21፣2016 - የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የ60 ሚሊዮን ብር አክሲዮን መግዛቱን ተናገረ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የ60 ሚሊዮን ብር አክሲዮን መግዛቱን ተናገረ።


ባንኩ ከገበያው የ60 ሚሊየን ብር ድርሻ የገዛው በትናንትናው ዕለት መሆኑን ለሸገር በላከው መግለጫ ተናግሯል

በዚህም የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ የገበያው መስራች አባል መሆን ችሏል።


ባንኩ የ60 ሚሊዮን ብር ድርሻ ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የገዛው ገበያው በሀገሪቱ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ተጨማሪ የፋይናንስ እድሎችን ለመፍጠር የተቋቋመ መሆኑን በመገንዘብ ነው ብሏል።


ባንኩ የገዛው አክሲዮን ለህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ ልማት የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመደገፍ በኩል ትልቅ ሚና ይኖረዋል ሲልም በመግለጫው አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ከእቅዱ ቀድሞ ለማሰባሰብ ካቀደው የመመስረቻ ካፒታል 1 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን መናገሩ ይታወሳል፡፡


መስራች የሚያደርገው የአክሲዮን ሽያጭ ቀነ ገደብ በትላንትናው እለት አብቅቷል፡፡


ገበያው በቅርቡ ስራ ይጀምራ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች፣ የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማሰባሰብና ሌሎች ዘመናዊ የግብይቶችን ለማካሄድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




bottom of page