top of page

መጋቢት 20፣2016 - አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የ 90.6 ሚሊዮን ብር ድርሻ ገዛ።

የ90.6 ሚሊዮን ድርሻውን ግዥ የተፈራረሙት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጫንያለው ደምሴ እና የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል ናቸው።

 

አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ 10 በመቶ ወይንም የ90.6 ሚሊዮን ድርሻ መግዛቱ የተናገሩት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጫንያለው ደምሴ  ገበያው ስራ እንዲጀምር በነበረው ሂደት ባንኩ ተሳታፊ መሆኑን ተናግረዋል።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ የፋይናንስ ውስንነት በመኖሩ የኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን የተናገሩት አቶ ጫንያለው በሀገሪቱ ሙዓለ ነዋይ  መጀመሩ ጥቅሙ ይህ ነው የሚባል አይደለም ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ  ጥላሁን እስማኤል ባንኮች አሁን ካላቸው አቅም የበለጠ እንዲኖራቸው እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ካፒታል ገበያውን መቀላቀል አለባቸው ብለዋል።

 

የፋይናንስ ተቋሞች ከሰነድ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ድርሻ መግዛታቸውም፤ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የካፒታል ገበያ የሚያበረታታ ነው ሲሉ ስራ አስፈፃሚው  አስረድተዋል።

 

ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

bottom of page