መንግስት እድሜው ለጡረታ ለደረሰ ዜጋ ሁሉ ጡረታ እንዲከፍል ተጠየቀ፡፡
- 4 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 19/ 2018
መንግስት እድሜው ለጡረታ ለደረሰ ዜጋ ሁሉ ጡረታ እንዲከፍል ተጠየቀ፡፡
ይህንን የጡረታ ወጪ ለመሸፈን ገንዘቡ ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች መሰብሰብ አለበትም ተብሏል፡፡
ጥያቄውን ያቀረበው የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማህበር መሆኑን ሰምተናል፡፡
እስካሁን ያለው አሰራር ከተቀጣሪ ሰራተኞች ውጭ ያሉ በእድሜ የገፉ ሰዎችን የማያካትት መሆኑ ተገቢ አይደለም ያሉን የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማህበር ምክትል የቦርድ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ክፍሉ፤ በየትኛውም የስራ መስክ የተሰማራ ግለሰብ ሃገሩን ሲያገለግል እንደመቆየቱ በማምሻ እድሜው ጡረታ ሊከፈለው ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ማህበራቸው ዝርዝር አተገባበሩን የሚያስረዳ ሰነድ አዘጋጅቶ ለመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደርና ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስገባቱንም ጠቁመዋል፡፡
ወደ እዚህ የሰነድ ዝግጅት እንድታመሩ ያደረጋችሁ ምንድነው? ያልናቸው አቶ ጌታቸው ከጡረታ ውጪ የሆኑ አረጋውያን እንደከዚህ ቀደሙ በቤተሰብ የተከበቡ አይደሉም፤ በኑሮ ውጣ ውረድ ምክንያት ልጆቻቸው ትተዋቸው ወደ ራሳቸው ኑሮ እየገቡ ነው፤ በዚህም ምክንያት በባዶ ቤት ያለ ጧሪ እየቀሩ በመሆኑ ይህንን ችግር በጥቂቱም ቢሆን ለማቃለል ነው ብለውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ.....
ምንታምር ጸጋው





Comments