top of page

መስከረም 9 2018 - የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 20 እስከ 22 እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Sep 19
  • 1 min read

የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ለ5ተኛ ጊዜ ከመስከረም 20 እስከ 22 ድረስ አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ተናገረ።


የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ወዳጆ በሰጡት መግለጫ፤ ከዚህ በፊት የተካሄዱት የቱሪዝም ሳምንቶች የክልሉን ቱሪዝም በተገቢው መንገድ ለማስተዋወቅ አግዘዋል ብለዋል።


በዘንድሮው የቱሪዝም ሳምንት የሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳን ጨምሮ የ6 ሀገራት የቱሪዝም ባለሞያዎችና አስጎብኚ ማህበራት እንደሚካፈሉ ጠቅሰዋል።

ree

የቱሪዝም ሳምንቱን አስመልክቶ በሚዘጋጀው ኤግዚቢሽን ከውጪ የሚመጡ የ6ቱ ሀገራት ተሳታፊዎች ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ ተሳታፊዎች የቱሪዝም ምርቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።


የፓናል ውይይት ይካሄዳል የተባለ ሲሆን የኦሮሚያ ቱሪዝም አዋርድ እና ሚስ ኦሮሚያም በቱሪዝም ሳምንቱ ይቀርባሉ ተብሏል።


አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ላይ በሚደረገው የኢሬቻ በዓል ላይ አስጎብኚ ማህበራት ወደፊት ይህንን ያማከለ የቱሪዝም ፓኬጅ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ በዚህ ዓመት ምክክርና ጉብኝት ይደረጋል ሲል የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ተናግሯል።


ለ5ተኛ ጊዜ በሚደረገው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙትን በስፋት ለማስተዋወቅ ታቅዷል ሲል ኮሚሽኑ አስረድቷል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page