top of page

መስከረም 9 2018 - የሕፃን እና የወላጅ ትስስርን የሚቆጣጠር የነርቭ ዘዴን ሳይንቲስቶች ማገኘታቸው ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Sep 19
  • 1 min read

የእስራኤል ተመራማሪዎች ኦክሲቶሲን የተባለ የአንጎል ኬሚካል ህፃናት ከወላጆቻቸው የሚለዩበትን ሁኔታ እንዲቋቋሙ እንደሚረዳቸው አረጋግጠናል አሉ።


ግኝቱ በህጻናት እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ያሳያል ሲል ዌይዝማን የሳይንስ ተቋም ተናግሯል ። ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ የኦክሲቶሲን እንቅስቃሴ ህጻናት ከእናታቸው ሲለዩ በአእምሮ ውስጥ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ አረጋግጠናል ብለዋል።


ኦክሲቶሲን ብዙ ጊዜ "የፍቅር ሆርሞን" ተብሎ ይጠራል። ምክንያቱም ማህበራዊ ትስስርን ለመፍጠር ስለሚረዳ ተብሏል። አዲሱ ጥናት እንደሚያሳየው ኦክሲቶሲን ከሰው ልጅ ባሻገር ገና በተወለዱ እንስሳት ስሜታዊ ባህሪ ላይም ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ነው።


በጥናቱ ወቅት የኦክሲቶሲን ስርዓት ያላቸው ጨቅላ ህጻናት ከእናታቸው በሚለያዩበት ጊዜ አምርረው ያለቀሱ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ የኦክሲቶሲን ስርዓት የሌላቸው በቀላሉ መላመዳቸውን አስረድተዋል ።


ኦክሲቶሲን ህጻናት ከእናታቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ የሚያሳዩት ባህሪ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ጥናቱ አሳይቷል።

ree

የተመራማሪዎች ቡድን በሴቶች እና በወንዶች መካከል ልዩነቶችን ማግኘታቸውን ጠቁመው ሴት ህጻናት በኦክሲቶሲን እንቅስቃሴ ላይ በተደረጉ ለውጦች የበለጠ መጎዳታቸውን አረጋግጠዋል። ይህም ስሜታዊ እድገት ቀደም ሲል ከታሰበው በላይ በጾታ መካከል ልዩነት ሊፈጥር እንደሚችል ይጠቁማል ብለዋል።


ጥናቱ ከዚህ ቀደም ባሉ የህይወት ተሞክሮዎች ፣ የአዕምሮ ስርዓትን እና ማህበራዊ ባህሪን እንዴት እንደሚቀርጹ አዲስ ግንዛቤ እንደሚሰጥ ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል።


እንደ ኦቲዝም ባሉ ሁኔታዎች ላይ ለወደፊቱ ምርምር ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል ገልጸዋል ሲል የቻይናው ሚዲያ ሺኑዋ ዘግቧል።


ትዕግሥት ፍሰሃ





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page