መስከረም 9 2018 - አስረኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ህዳር ወር ላይ በሠመራ ሎጊያ ከተማ እንደሚካሄድ ተነገረ።
- sheger1021fm
- Sep 19
- 1 min read
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሣኒ ፎረሙን አስመልክተው ዛሬ በመስሪያ ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ስጥተዋል።
በመግለጫቸውም አስረኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ከህዳር 6 እስከ 10 ቀን 2018 ዓም በአፋር ክልል ይካሄዳል ብለዋል።
በፎረሙ ላይ ከ150 እስከ 200 የሚደርሱ ከተሞች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የልምድ ልውውጥ በከተሞች መካከል ይኖራል የተባለ ሲሆን ጥናቶችና ምርምሮች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸውም ተጠቅሷል።
እያንዳንዱ ከተማ የሠራውን ስራና ያገኘውን ውጤት የሚያሳይበት ኤግዚቢሽንም እንደሚኖር ሚኒስትሯ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል።
የዘንድሮው የከተሞች ፎረም በአፋር ክልል የሚካሄደው "የከተሞች ዕድገት ፣ ለኢትዮጵያ ልህቀት"በሚል ሀሳብ እንደሆነም ተነግሯል።
ፎረሙን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከአፋር ክልል መንግስት ጋር በመተባበር ያዘጋጁታል ተብሏል ።
ዘጠነኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም አምና በሶዶ ከተማ ነበር የተዘጋጀው።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments