top of page

መስከረም 8 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Sep 18
  • 2 min read

በግብፅ ከካይሮ ቤተ መዘክር ጥንተ ጥንታዊ የወርቅ አምባር መጥፋቱ ለአገሪቱ ሰድዶ ማሳደድ ሆኖባታል ተባለ፡፡


ከቤተ መዘክሩ የጠፋው የወርቅ አምባር የ3 ሺህ አመታት እድሜ ያለው ጥንታዊ ጌጥ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ጥንታዊው የወርቅ አምባር የጠፋው ከቤተ መዘክሩ የጥንታዊ ቅርሶች ማደሻ ክፍል ነው ተብሏል፡፡

ree

የጥንታዊውን የወርቅ አምባር ምስል የያዘ ሰሌዳ በየኤርፖርቱ እና በየወደቡ ለጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች እና ለፀጥታ አስከባሪዎች መሰራጨቱ ታውቋል፡፡


ሰሌዳው የጉምሩክ ተቆጣጣዎቹ እና የፀጥታ አስከባሪዎች ይሄን መሰሉን አምባር የያዙ ሰዎች ካጋጠሟቸው በጭራሽ እንዳያሳልፉ ለማስጠንቀቅ መሰራጨቱ ተጠቅሷል፡፡


የካይሮው የጥታዊ ቅርሶች ቤተ መዘክር በመካከለኛው ምስራቅ እድሜ ጠገቡ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡



ሳውዲ አረቢያ እና ፓኪስታን ጥቃትሽ ጥቃቴ ነው ተባባሉ፡፡


ሁለቱ አገሮች የጋራ መከላከያ የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


ሳውዲ አረቢያ እና ፓኪስታን በዚሁ የጋራ የመከላከያ ስምምነታቸው በ3ኛ አገር በአንዷ አገር ላይ የሚፈፀም ጥቃት በሁለቱም ላይ የተፈፀመ ያህል እንደሚቆጥሩት ተጠቅሷል፡፡


የጋራ መከላከያ የትብብር ስምምነት በሳውዲው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን እና በፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህቫዝ ሻሪፍ በሪያድ መፈረሙ ታውቋል፡፡


ሁለቱ አገሮች የቆየ ጥብቅ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው መረጃው አስታውሷል፡፡



በቻይና ሁለት በምድር ተሽከርካሪ በሰማይ በራሪ መኪኖች በአየር ላይ ተጋጭተው ተከሰከሱ፡፡


በሰማይ በራሪ፣ በምድር ተሽከርካሪ የሆኑት የቴክሎጂ ውጤቶች እንደተጋጩ በእሳት ተያይዘው እንደተከሰከሱ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ሰው አልባዎቹ በሰማይ በራሪ በምድር ተሸከርካሪ የቴክሎጂ ውጤቶች የተላተሙት በልምምድ ማሳያ ወቅት ነው ተብሏል፡፡


በግጭቱ በሰዎች ላይ ያጋጠመ አንዳችም ጉዳት እንደሌለ የፈጠራ ባለቤቱ ኩባንያ የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡


የበረራ አካላቱ ግጭት የደረሰው በቻንግቸን የአየር ትርዒት ማሳያ ስነ ሥርዓት ወቅት መሆኑ ታውቋል፡፡


በሰማይ በራሪ እና በምድር ተሽከርካሪ የሆኑት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሙከራቸው በተገቢው ሁኔታ እንደተጠናቀቀ በ300,000 ዶላር እነሆ ለገበያ እንደሚባሉ መረጃው አስታውሷል፡፡



የማሊ ፅንፈኛ አማጺያን ከሴኔጋል እስከ ማሊዋ ርዕሰ ከተማ ባማኮ በሚዘልቁት አውራ ጎዳናዎች በሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚጥሉት አደጋ እየጨመረ ነው ተባለ፡፡


ወደ ማሊ እንደ ነዳጅ ዘይት ያሉ ጠቃሚ ምርቶች የሚገቡት በነዚሁ አውራ ጎዳናዎች ተጓጉዘው እንደሆነ ቢቢሲ አስታውሷል፡፡


አሁን ግን ፅንፈኛ ታጣቂዎች ከሴኔጋል በሚመጡት እና ወደ ሴኔጋል በሚያመሩት ተሽከርካሪዎች እና ሾፌሮቻቸው ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እየተባባሰ ነው ተብሏል፡፡


ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡


የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥቃት ባየለባቸው አውራ ጎዳናዎች የፀጥታ ቁጥጥሩ እንደሚጠብቅ ተናግረዋል፡፡


ከማሊ በተጨማሪ እንደ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ያሉ አገሮችም የፅንፈኞች ተፅዕኖ የበረታባቸው እንደሆኑ መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page