መስከረም 8፣2017የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት፤ ኢትዮጵያ በይፋ አስመረቀች
- sheger1021fm
- Sep 18, 2024
- 1 min read
የቱሪዝም ሳተላይት አካውንቱ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከቱሪዝሙ ምን ያህል ገቢ ታገኛለች፣ ምን ያህል ሰው አዲስ ስራ ተፈጥሮለታል፣ ምን ያህል ጎብኚስ በየዓመቱ ወደ ሀገሪቱ መጥቷል የሚለው ትክክለኛ መረጃ ለማወቅ የሚረዳ ነው ተብሏል።
ይህም ፖሊሲዎች ለማውጣትና የወደፊት የቱሪዝም ዘርፍ እቅዶች በትክክለኛ መረጃ ለማውጣት ይረዳል መባሉን ሰምተናል፡፡
ይፋ የተደረገው የቱሪዝም ሳታላይት አካውንት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዲያድግም መረጃ በመስጠት ይረዳል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ''ኦሪጅንስ ትራቭል ማርት'' የተሰኘ የቱሪዝም አውደ ርዕይ ዛሬ የተከፈተ ሲሆን በየዓመቱ አውደ ርዕዩን ለማዘጋጀት እቅድ መያዙ ተሰምቷል።
ኢትዮጵያ ኦሪጅንስ ትራቭል ማርት የሚል አለማቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን መለያ ለመፍጠር ያለመች ሲሆን አውደ ርዕዩ የንግድ ለንግድ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የዘርድሮው ኤግዚቢሽን የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(IGAD) አባል ሀገራት ብቻ የተሳተፉበት ሲሆን ወደፊት ሲካሄድ ግን ከየትኛውም የአለም ክፍል ያሉ የቱሪዝም ንግድ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችና ሀገራት እንዲሳተፉበት ታስቧል ተብሏል፡፡
የIGAD አባል ሀገራት የቱሪዝም ማስተር ፕላን በጋራ ተዘጋጅቷል የተባለ ሲሆን ይህም ሀገራቱ ቱሪዝማቸውን ለማሳደግና በፋይናንስ ዘርፉ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ይረዳቸዋል መባሉን ሰምተናል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ያዝጋጀው የኦርጅንስ ትራቭልስ ማርት የቱሪዝም አውደ ርዕይ በአድዋ ሙዝየም የከፈተ ሲሆን አውደ ርዕዩ ለ3 ቀን እንደሚቆይ ሰምተናል።
በረከት አካሉ












Comments