መስከረም 7 2018 - የመሬት አጠቃቀም ረቂቅ ፖሊሲ ዝግጅት መጠናቀቁን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Sep 17
- 1 min read
ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ድረስ #የመሬት_አጠቃቀም_ፖሊሲ እንደሌላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡
የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ ሀገሪቱ ባለማውጣቷ ምን ዓይነት ችግሮች እንደተፈጠሩ በዝርዝር የሚለይ ጥናት ተሰርቶ ረቂቅ ፖሊሲ መሰናዳቱን በግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ትግስቱ ገብረመስቀል ተናግረዋል፡፡
በዚህም የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ ባለመኖሩ ምክንያት ለግብርና መዋል የነበረበት ለም መሬት ለኢንዱስትሪዎች፣ ለመንገድ፣ ለመጋዘኖች እና ለመኖሪያ ቤት ማስፋፊያ እንዲውሉ ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
(ተያያዥ ዘገባን ለማንበብ…. https://tinyurl.com/2rxvhs6w )
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments