መስከረም 5 2018 - የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ተፈታኞች የሚያገኙባቸውን አድራሻዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
- sheger1021fm
- Sep 15
- 1 min read
የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ተፈታኞች የሚያገኙባቸውን አድራሻዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
ተፈታኞች ውጤታቸውን በዌብ ሳይት፤ በቴሌግራም ወይም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል አገልግሎቱ፡፡
አድራሻዎቹም ለዌብ ሳይት፡ result.eaes.et
ለቴሌግራም፡ t.me/EAESbot እና
አጭር የጽሑፍ መልዕክት 6284 መሆናቸውን አመልክቷል።
ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራዎችን የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ መውሰድ(download በማድረግ) እና መጠቀም ይችላሉ ብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s








