top of page

መስከረም 30 2018 - ''የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ምደባ ቀስ በቀስ ይቆማል ያሉት'' ብርሃኑ ነጋ ፕ/ር

  • sheger1021fm
  • Oct 10
  • 1 min read

ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸው ትክክለኛ መረጃ ካላቀረቡ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሀላፊዎቻቸው ከስራ ይባረራሉ ተባለ።


ይህንን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።


በቀጣይ 6 ወራት ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ሌሎችም ጉዳዮች መረጃ በትክክል ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ አለባቸው ተብሏል።


ይህንን ያላደረገ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በስራው አይቀጥልም ብለዋል።


ይህንን ስራ እኔ በቀጥታ እከታተለዋለሁ ሲሉም የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ree

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የዩኒቨርስቲ ውጤት በተመለከተ የስምምነት ውል በተፈራረመበት ወቅት ነው።


የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ምደባ ቀስ በቀስ ይቆማል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ ዩኒቨርስቲዎች በራሳቸው ጥረት ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል።


በቅርብ ጊዜ ውስጥ እኛ የተማሪ ምደባ ስራን እየቀነስን እንመጣለን፣ ያ ሲሆን ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ መርጠውና በተቋሙ ብቃት ለይተው መግባት ይጀምራሉ ብለዋል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page