top of page

መስከረም 30፣2016 - የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ 3 የአፍሪካ ሀገሮችን አስጠነቀቃቸው


የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ 3 የአፍሪካ ሀገሮችን አስጠነቀቃቸው፡፡


ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የአለም ባንከ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ኡጋንዳንና ናይጄሪያ መሆናቸውን ዘ ቴሌግራፍ ፅፏል፡፡


የዓለም ባንክ ሀገሮቹን በብርቱ ያስጠነቀቃቸው የገንዘብ ፖሊሲያቸውን ሊያበላሹ ከሚችሉ አደገኛ ውጥኖች እንዲታቀቡ ነው፡፡


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኡጋንዳና የናይጀርያ ማዕከላዊ ባንኮች የገንዘብ ፖሊሲያቸው በክፉ ሊያዳክምባቸው ከሚችሉ ጉዞዎች እጃቸውን አንዲሰበስቡ አስጠንቅቋቸዋል፡፡


የየሀገራቱ መንግስት የቀጥታ የብድር ጣልቃ ገብነት፣ ዘርፍ ያልለየ የመንግስት ድጎማዎች ፣ የውጭ ምንዛሪና አስተዳደር እና ቁጥጥር ላይ በብርቱ መንገዳቸውን እንዲፈትሹ ተመክረዋል፡፡

የአለም ባንክ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳና ናይጀሪያ ያጋጠማቸውን የዋጋ ንረትን ለመመከት በገንዘብና በገንዘብ ነክ ወይም በሞኒተሪና ፊስካል ፖለሲያቸው መሀል የተናበበ ስራ መስራት እንዳለባቸው ጠበቅ አድርጎ እንዳስረዳቸው ተሰምቷል፡፡


አለም ባንክ ይህንን ችግር ለማስተካከልም የሀገር ውስጥ እምቅ ሐብቶችን ማገላበጠና ወደ ስራ ማስገባት እንደሚስፈልግ አስረድቷል፡፡


የተለመደው የግብር ወይም ታክስ አሰባሰብ ላይ ችክ ከማለት አዳዲስ አሰራርና የታክስ አሰባሰብ ስራ ላይ ለውጥ ማድረግ እንደሚያግዝም መክሯል፡፡


የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እና ልማትን ለማስፋፋት የሀገር ውስጥ ሃብት ማሰባሰብ፣ ቀልጣፋ ወጪ እና የታክስ ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ባንኩ አሳስቧል።


እንዲህ ያለ ፈተና ያጋጠማቸው አገሮች በሀገር ውስጥ የሚደረገው የግብር አሰባሰብ ለውጥና ማሻሻያ በዲጂታል መንገድና በቴክኖሎጂ አስደግፈው ወደ ስራ ስለቀየሩት አግዟቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡


የግብር አሰባሰብንና እና የድጎማ ማሻሻያዎችን በመተግበር እና ለታክስ አስተዳደር እና ተገዢነት ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንደሚገባም ባንኩ አስረድቷል፡፡



ተህቦ ንጉሴ



የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page