top of page

መስከረም 28 2018 - የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የመጀመሪያ የሆነው ቅርንጫፍ ዛሬ አገልግሎት ጀምሯል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 8
  • 1 min read

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የመጀመሪያ የሆነውን ቦሌ ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት አገልግሎት አስጀምረዋል::


የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በ12 የከተማው ተቋማት ስር ያሉ 96 አገልግሎቶች በጋራ አገልግሎት የሚሰጡበት መሆኑንና ሁለት ባንኮች እና 4 የፌደራል ተቋማትም መካተታቸውን አስረድተዋል::

ree

በቅርቡ ሶስት የፌደራል ተቋማትን ወደ ማዕከሉ እንደሚያካትት እና በቀጣይ 9 ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት እንዳቀደም ሰምተናል::


የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቅልጥፍና፣ የደንበኞችን እርካታ ይጨምራል ተብሎ ታምኖበታል፡፡


አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች በዲጂታል እና በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአንድ ማዕከል ውስጥ እየሰጡ እንደሆነም ሰምተናል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page