መስከረም 28 2018 11ኛው የአፍሪካ አሰላሳዮች (ቲንክ - ታንክ) ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 8
- 1 min read
ጉባኤው"ከግብር ወደ ተግባር" በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ የጀመረ ሲሆን እስከ ከነገ ወዲያ ድረስ ይቆያል፡፡
በሶስት ቀናቱ ውሎ በአፍሪካ በህዝብ ሀብት አስተዳደር ላይ ያሉ የፖሊሲ አፈጻጸም ችግሮች ላይ ይመክራል፣ ሀሳብ ይዋጣል ተብሏል፡፡
300 አሰላሳዮች ( #Think_Tank ) ፖሊሲ አውጪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የግሉ ዘርፍ መሪዎች፣ የልማት አጋሮች ከ50 ሀገራት ተወክለው እየተሳተፉ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

አፍሪካ እንዴት አድርጋ ያለ ውጭ ጣልቃ ገብነት ሀብቷን ታስተዳድር፣ እንደ ታክስ ያሉ ህጎችን ታውጣ፣ እንዴትስ አድርጋ ወጪዎችን ትቻል አንዲሁም እዳዋልን ትከፍላለች በሚሉት ነጥቦች፣ በፖሊሲ ቁረጠኝነትና አፈጻጸም መካከል ያለውን ክፍተት መድፈን ይቻላል የሚሉት የጉባኤው መወያያ ጉዳዮች መሆናቸውን ተነግሯል፡፡
የህዝብ ሀብት ለማስተዳደር ፈተና ሆነው የቀጠሉ የፖሊሲ ማነቆዎች እንዴት መፈተታት አለባቸው፣ የውጭ እርዳታ ጥገኝነትን መቀነስ እንዲሁም አጀንዳ 2063 እና ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት የሚያስፈልጉትን ሀብቶች ለማሰባሰብ ምን ማድረግ ይገባል የሚሉትም የጉባኤው የትኩርት ጉዳዮች ናቸው፡፡
ጉባኤውን የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን(ACBF) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) እና የአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር አንዳዘጋጁት ሰምተናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ












Comments