መስከረም 23 2018 - በነዳጅ የሚሰሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር አይገቡም ተባለ
- sheger1021fm
- Oct 3
- 1 min read
በነዳጅ ሀይል የሚሰሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ አይገቡም ተባለ።
በዚያ ምትክ በ #ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚያስገቡ የቀረጥ ነፃ እድል ይሰጣል ተብሏል።
ይህንን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር ውስጥ በስራ ላይ ያሉ 2,000 የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችም ከነዳጅ ተጠቃሚነት ወደ ጋዝ እንዲቀየሩ የማድረግ ስራ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይሰራል ብለዋል።
ትናንት 111 ሚሊየን ሊትር የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት አቅም ያለው የካሉብ የጋዝ ማምረቻ ስራ መጀመሩ ተነግሯል።
በሁለተኛ ምዕራፍ ከመጀመሪያው 12 እጥፍ አቅም ያለውና 1.33 ቢሊየን ሊትር ጋዝ የሚያመርተው ፕሮጀክት ስራ መጀመሩ ተነግሯል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments