መስከረም 22 2018 -የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
- sheger1021fm
- Oct 2
- 1 min read
የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው ተብሏል።
የመሰረት ድንጋዩን መቀመጥ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ፅሁፍ ዛሬ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያኮራ ታሪካዊ ሁነት ተፈፅሟል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ የሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካን መሠረት አስቀምጠናል ብለዋል።
የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው ተብሏል።
የማዳበሪያ ፋብሪካው ደግሞ ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፅሁፋቸው።
እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢንደስትሪ እድገትን ከማሳየት በላይ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እድሎችን የመጠቀም፣ ትብብርን የማጠናከር እና ሰላምን የማጽናት የጋራ ኃላፊነት ማሳያ ናቸው ብለዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx








