መስከረም 22 2018 - እንደ መሬት ፅ/ቤት ያሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተገልጋዩን በማንገላታት ብዙውን ጊዜ ይወቀሳሉ፡፡
- sheger1021fm
- Oct 2
- 1 min read
እንደ መሬት ፅ/ቤት ያሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተገልጋዩን በማንገላታት ብዙውን ጊዜ ይወቀሳሉ፡፡
የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቅልጥፍና ይጨምራል፣ የደንበኞችን እርካታ ይጨምራል በሚል የአንድ መሶብ አገልግሎት ተጀምሯል፡፡
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች በዲጂታል እና በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአንድ ማዕከል ውስጥ እየሰጡ እንደሆነም ሰምተናል፡፡
13 ተቋማትን ይዞ የጀመረው ማዕከሉ 107 አገልግሎቶች እንዳሉትም ሰምተናል፡፡
13ቱ ተቋማት በሶስት ዘርፍ የተከፈሉ እንደሆኑና በዚህም የኢኮኖሚ ዘርፍ፣ የቤቶችና ትራንስፖርት ዘርፍ፣ እንዲሁም የመሬት እና ግንባታ ዘርፍ እንደሆኑ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
የመሶብ ሲስተም እዚሁ ሃገር ውስጥ በኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀስ ኢንስቲትዩት የለማ ነው ተብሏል፡፡
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ የቀደሞ አራዳ ክ/ከተማ የነበረበት ህንጻ ላይ ነው፡፡
ወደፊት ዘጠኝ ቅርንጫፎችን እንደሚከፍት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
ማርታ በቀለ












Comments