top of page

መስከረም 20 2018 - አቢሲኒያ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት 10.1 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አገኘሁ አለ

  • Sep 30, 2025
  • 1 min read

ይህም ካለፈው የሒሳብ ዓመት የ91.4 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን ተናግሯል።

አቢሲኒያ ባንክ ይህንን የተናገረው 29ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው።


በተጠናቀቀው የሒሳብ አመት ባንኩ ያገኘው የውጭ ምንዛሬ መጠን 663 ሚሊየን ዶላር መሆኑን የተናገረ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ56.4 ጭማሬ አሳይቷል ብሏል።


አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም ከ192.5 ቢሊዮን ብር ወደ 243.2 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏል የተባለ ሲሆን ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ውስጥ የቁጠባ ሒሳብ ድርሻ 65.2 በመቶ መያዙ ተነግሯል።


ከወለድ ነፃን ሳይጨምር ለደንበኞች የሰጠሁት ብድር 193.4 ቢሊየን ብር ደርሷል ማለቱን በሪፖርቱ የሰማን ሲሆን ካለፈው ሒሳብ ዓመት የብድርና ቅድመ ክፍያዎች ጋር ሲመሳከር የ30.5 ቢሊዮን ብር ጭማሬ እንዳለው ተነግሯል።

ባንኩ ካለው የብድር ክምችት ውስጥ የወጭ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና የሀገር ውስጥ ንግድ የሥራ ዘርፎች 64.2 በመቶውን ይሸፍናል መባሉ ሲነገር ሰምተናል።


በ2017 የሒሳብ አመት የአቢሲኒያ ባንክ ጠቅላላ ወጭ 29 ቢሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡ በሪፖርቱ የተነገረ ሲሆን  ጠቅላላ ሀብቱም 286.2 ቢሊዮን ደርሷል ተብሏል።


በተጠናቀቀው በጀት አመት የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ወደ 28.8 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን የሰማን ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የ5.7 ቢሊዮን ብር ወይም የ24.4 በመቶ እድገት አለው ተብሏል።


እንዲሁም የባንኩ የተከፈለ ካፒታል መጠን ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው 14.2 ቢሊዮን ብር ወደ 15 ቢሊዮን ብር በማደግ 794 ሚሊዮን ወይም የ5.6 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1


Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page