top of page

መስከረም 19 2018 - የ2018 የኢሬቻ በዓል የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ፣ በቀጣዩ ቀን እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ እንደሚከበር ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Sep 29
  • 1 min read
ree

በዓሉ ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት በሚል ሀሳብ ይከበራል ተብሏል።


የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በበዓሉ አከባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ስቴዲየም በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማዕከል ለጋዜጠኞች እየሰጠ ነው።


ኢሬቻ የምስጋና እና የዕርቅ በዓል ነው ያሉት የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በአከባባሩ ላይ ሰዎች በሃይማኖት ፣ በብሄር ፣ በፆታ ወዘተ ልዩነት እንደማይደረግባቸውም ተናግረዋል ።


የኢሬቻ በዓል ከማህበራዊ ቱሩፋቶቹ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታም ያለው ነው ብለዋል ።


የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሩ በበኩላቸው በዓሉ ዕሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page