top of page

መስከረም 16 2018 - ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክሌር ልማት ፕሮጀክት ስምምነት መፈራረማቸው ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Sep 26
  • 1 min read
ree

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ልማት ዙሪያ በሮሳቶም እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የድርጊት መርሃ ግብር ተፈራረመዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።



የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሲ ሊካቼቭ እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የተፈረመውን ሰነድ ተለዋውጠዋል።



በዝግጅቱ ላይም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተገኝተዋል ።



ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሩሲያ የሄዱት በዓለም የአቶሚክ ሣምንት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ መሆኑ ተነግሯል።



ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የኒውክለር ኃይልን በጥንቃቄ በማቀድና ጥቅም ላይ በማዋል ጠንካራ የሀገር ውስጥ አቅምን በመፍጠር ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም ማቀዷን አስረድተዋል ።



የሩሲያን የኒውክለር ጠበበቶች ከኢትዮጵያ የተማረ ሰው ሃይል ጋር በማጣመር ለሕዝብ የሚጠቅምና ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነ የኒውክለር ቴክኖሎጂ ለመገንባት መታቀዱን ጠቅሰዋል ፡፡



ከዚሁ ወሬ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።



መሪዎቹ የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስረድቷል።



ውይይቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ንፁህ ኃይል ምንጭ የሚውል የጋራ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ የማልማት ስምምነቶችን ጨምሮ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ መካሄዱም ተነግሯል።



ኢትዮጵያ ለሰላማዊ አለማ የሚሆን የኒውክለር ፕላት እንደምታቋቁም በአደስ አመት ዋዜማ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።



ይህንን የኢትዮጵያ ፍላጎትም የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ኤጀንስ ይደግፈዋል መባሉ ይታወሳል።



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…







Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

1 Comment


Anika sharma
Anika sharma
Sep 29

It was immediately evident that she wasn’t Escort in Indore only stunning but also thoughtful, graceful, and considerate, making sure every detail of our time was tailored perfectly to my enjoyment.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page