top of page

መስከረም 16 2018 - በአዲስ አበባ ከተማ በየቀኑ ከአንድ በላይ የግንባታ ሰራተኛ ሕይወት እንደሚያልፍ የከተማዋ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Sep 26
  • 2 min read
ree

በአዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ከ24 ሺህ በላይ ህንጻዎች በግንባታ ላይ መሆናቸው ተነግሯል ።

የአዲስ አበባ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሕይወት ሳሙዔል በግንባታ ሂደት ላይ በከተማዋ እየደረሰ ያለው የሞት እና የአካል ጉዳት አሳሳቢ እንደሆነ አስረድተዋል ።


እነዚህም ጉዳቶች በአግባቡ ሪፖርት ሳይደረጉ እየታለፉ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ በከተማዋ እየተገነቡ ካሉ እና ከተገነቡ ህንጻዎች ጀርባ የብዙ እህቶቻችን እና ወንደሞቻችን ደም ፈሷል ፣ ሕይወትም ጠፍቷል ብለዋል።


ከ2015 እስከ 2017 አመታት ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ሂደት ላይ የነበሩ 142 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ደግሞ የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር አበበ እሸቱ ናቸዉ ።


ይህ ለፖሊስ ሪፖርት ከተደረገ እና ከጤና ተቋማት የተሰበሰበ መረጃ ስለሆነ እንጂ በከተማዋ በግንባታ ሂደት ላይ እየደረሰ ያለውን ሞት የማያመላክት መረጃ እንደሆነ መታወቅ አለበት ብለዋል ምክትል ዳይሬክተሩ።


ምክንያቱም ለፖሊስ ሪፖርት ሳይደረግ የሚቀር፣በሽምግልና ፣በመሽፋፈን እና አስታምማለው በሚል በየቤቱ የሚሞተው ሰራተኛ ሪፖርት የተደረገውን በቡዙ ስለሚበልጥ ነው ብለዋል።


የኮንስትራክሽን ስራ መስክ ከግብርና በመቀጠል ከፍተኛ የስራ እድል ፈጣሪ መሆኑን የተናገሩት አበበ እሸቱ በግንባታ ስራ ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ግን አሰቃቂ ሞት እና የአካል ጉዳት እየደረሰ እንደሆነ አስረድተዋል ።


በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በ2017 ዓ.ም ለ11 ሺህ ግንባታዎች ፍቃድ እንደተሰጠ የተነገረ ሲሆን ከዚያ በፊት የቀጠሉ ከ12 ሺህ በላይ የህንጻ ግንባታዎች አሉ ይህም በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ያለውን ህንጻ ግንባታ ወደ 24ሺህ ያደርሰዋል ተብሏል ።


የእነዚህ ህንጻዎች አጠቃላይ ወጪም ወደ 500 ቢሊዮን ብር እንደሚጠጋ ኢንጂነር አበበ ተናግረዋል ።


መስኩ የስራ እድል በመፍጠር እና ኢኮኖሚውን በማንቀሳቀስ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ቢኖረውም በግንባታ ስራ ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ማለትም ከከፍታ ላይ በመውደቅ ፣የበሰበሰ እንጨት በመጠቀም ፣ለሊፍት እየተባሉ በሚተው ቦታዎች፣መከላከያ ባላመጠቀም ፣ኤሌክትሪክ ባለማጥፋት፣በቡለኬቶች እና ብረቶች ከህንጻዎች ላይ መውደቅ ምክንያት የሰው ሕይወት እየጠፋ እንደሆነ ምክትል ዳይሬክተሩ አስረድተዋል ።


ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህን አደጋ ለመቀነስ ቢያንስ ቢያነስ በግንባታዎች ላይ ያሉ ህንጻዎች ዝቅተኛ የደህንነት መስፈርት እንዲያሟሉ አያስገደደ እንደሆነ የተናገረ ሲሆን በዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት መሻሻል ማሳየታቸውን ተጠቁሟል።


የኢትዮጵያ ስራ ተቋራጮች ምህበር ፕሬዚዳንት ዩሱፍ ሙሃመድ በበኩላቸው መስኩ በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት እና አካል መጓደል ምክንያት እንደሆነ አብራርተዋል ።


ይህንን ጉዳት ለመቀነስ ደግሞ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል።


የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ስራ ተቋራጮች ማህበር፣የአዲስ አበባ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ፣የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣንእና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ተቋም በትናንትናው እለት በግንባታ ሂደት ደህንነት እና ጤና ላይ አብረው ለመስራት የጋራ ስምምነት አድርገዋል።


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page