መስከረም 15 2018 - ስለ ሀገሩ የማያውቅን ትውልድ ስለ ሀገር ፍቅር ማስተማር ውጤት ስለማያመጣ፤ ትውልዱ ሀገሩን እንዲያውቅ ብዙ ሥራ ይጠበቃል ተባለ
- sheger1021fm
- Sep 25
- 1 min read


ይህ የተባለው የቱሪዝም ሚንስቴር ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች ለተማሪዎችና መምህራን በሚያዘጋጁት ተንቀሳቃሽ የቱሪዝም አውደ ርዕይ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ነው።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚንስትርሯ ሠላማዊት ካሳ ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ለመፍጠር ለትውልዱ በቅድሚያ ሀገሩን ማሳወቅ አለብን ብለዋል።
በሀገራችን ለ38ኛ በዓለም ደረጃ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የቱሪዝም ቀንን በማስመልከት ይህ ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕይ ለአንድ ወር ያህል በአራት ትምህርት ቤቶች ይዘጋጃል ብለዋል።
በዚህ ለተማሪዎች በሚቀርበው ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕይ ላይ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣የሳይንስና ባህል ጅርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች፣ በቅርቡ በገበታ ለሀገር ፕሮጀት የተሰሩ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች፣ ጥንታዊ መዛግብቶች፣የተለዩ ጥብቅ ቦታዎች (የባዮስፌር ሪዘርቭ) የቱሪስት መዳረሻና ሌሎችም ተካታውበታል።
አውደ ርዕዩ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተከፍቷል።
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments