መስከረም 13 2018 - የት/ት ስራ ውስብስብ እና የብዙ ወገኖች ጥንካሬ የሚጠይቅ ነው ተባለ
- sheger1021fm
- Sep 23
- 1 min read
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውጤታማ ለማድረግ እና ብቁ ተማሪዎችን ለማብዛት በአንድ ተቋም ብቻ የሚከናወን አይደለም፤ የትምህርት ስራ ውስብስብ እና የብዙ ወገኖች ጥንካሬ የሚጠይቅ ነው ተባለ፡፡
በአሜሪካን ሀገር ከ45 ዓመታት በላይ በምህርት ስራ ላይ የተሰማሩትና በአሁኑ ወቅት ዶ/ር ነጋ የትምህርት ማዕከል በሚል በኦንላይን ት/ት የሚሰጡት ዶ/ር ነጋ ወርቁ የት/ት ሥርዓትን ለማዘመን የሁሉም ባለድርሻ ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ተማሪን ለማስተማር የትምህርት ሥርዓቱ እና ካሪኩለሙ ብቻውን በት/ት ሚኒስቴር በኩል የሚፈፀም አይደለም የሚሉት ባለሞያው ወላጆችን ጨምሮ የበርካታ ባለድርሻዎችን ድጋፍ ይፈልጋል ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments