top of page

መስከረም 13 2018 በቁጥር እየበዙ ያሉት የኢትዮጵያ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ መሆን ላይ ብዙ እንደሚቀራቸው ይነገራል።

  • sheger1021fm
  • Sep 23
  • 1 min read


የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በበኩሉ አዳዲስ ሃሳቦችን ስራ ላይ በማዋል ጭምር ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው የተመቹ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።


‎በኢትዮጵያ የከተሞች ቁጥር አጭር በሚባል ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።


ከአስር ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የከተሞች ቁጥር ከአንድ ሺህ አይበልጥም ነበር የሚለው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ አሁን ላይ ግን 2543 መድረሳቸውን ይጠቅሳል።


በርግጥ የከተማ አስተዳደር ደረጃ የደረሱት 275ቱ ብቻ መሆናቸውን ፤ ቀሪዎቹ ከ2000 ሺህ በላይ ከተሞች አሁንም ገና በማዘጋጃ ቤትደረጃ ያሉ መሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ አመልክቷል

በቁጥር እየበዙ ያሉት የኢትዮጵያ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸውስ ምን ያህል ምቹ ናቸው? የሚለውም  ጥያቄ ነው።


ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ ናቸው ሲባል ማሳያው ብዙ እንደሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ  ሣኒ ይናገራሉ።  ሁሉም ላይ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነውም ይላሉ ።

ree

ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ አዳዲስ አስተሳሰቦችን ጭምር እያስተዋወቅን ነው የሚሉት ሚኒስትሯ ፤   የሚከወኑ ስራዎችም ይህንኑ የሚደግፉ ስለመሆናቸው እንደሚረጋገጥ   ከተሞች ሲባል አብሮ የሚነሣው ሌላው ጉዳይ የመኖሪያ ቤት ችግር ነው ።


በከተሞች የቤት አቅርቦትን የማሳደጉ ስራ የፖሊሲ ለውጥ ጭምር ተደርጎበት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ፤ክልሎች በከተሞቻቸው ለሚኖሩ ሰዎች የመኖሪያ ቤት መገንባትን እንደ አንድ መሰረተ ልማት ስራ እንዲወስዱት መደረጉን ያነሳሉ።


የደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአትም አንዱ የከተሞች ዕድገት መለኪያ ሆኖ ይጠቀሳል።

ለነዋሪዎቻቸው ምቹ ናቸው አይደሉም ሲባል ይህም ከግምት እንደሚገባ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ  ሣኒ ተናግረዋል።


ከተሞች ባደጉ እና የሚጠበቅባቸውን ደረጃ ባሟሉ ቁጥር የሰዎችንም የአኗኗር ዘይቤ እንደሚቀይሩ የተናገሩት ሚኒስትሯ የተቀየሩ ሰዎች መልሰው ከተሞችን ይቀይራሉ ብለዋል።


በከተሞች የሚከናወን የትኛውም መሰረተ ልማት ፕላኑን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥም ሌላው የመንግስት ስራ ነው ተብሏል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page