top of page

መስከረም 13 2018 - ''ለመስቀል በዓል የምርት እጥረት እንዳያጋጥም እየሰራሁ ነው'' የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን

  • sheger1021fm
  • Sep 23
  • 1 min read

ከቀናት በኋላ ለሚከበረው የመስቀል በዓል የምርት እጥረት እንዳያጋጥም እየሰራሁ ነው ሲል የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ተናገረ፡፡


በተለይ ለበዓሉ በሰፊው የሚያስፈልገውን የስጋ አቅርቦት ለማሟላት እየሰራ መሆኑን ነግሮናል፡፡


በዚህም ከ200 በላይ በሚሆኑ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት #ልኳንዳ ቤቶች የስጋ አቅርቦት እንዲኖር አስቀድሞ እየተሰራ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ጌታቸው አንድ ኪሎ ስጋ እስከ 560 ብር እንዲሸጥ የዋጋ ተመን ወስነናል ብለዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ በባዕላት ወቅት ከ1200 በላይ የሚሆኑ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የመዝናኛ ተቋሞች ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ የምግብ፣ የመጠጥ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት መሰናዳታቸውን የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ፈሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page