መስከረም 12 2018 - በከምባታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (የማሳላ በዓል) እየተከበረ ነው፡፡
- sheger1021fm
- Sep 22
- 1 min read
በከምባታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (የማሳላ በዓል) እየተከበረ ነው፡፡
የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ የማሳላ እንግዶች ተገኝተው በዋናነት እየተከበረ ያለው በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ነው፡፡
በዓሉ ትናንት የጀመረ ሲሆን በዛሬው እለትም በከምባታ ሁለገብ ስቴዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች ቀጥሏል።

በከምባታ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የማሳላ በዓል በናፍቆት የሚጠበቅና በከፍተኛ ዝግጅት የሚከበር በዓል ነው ተብሏል፡፡
የብሔሩ ተወላጆች በማሳላ በዓል በግጭት ውስጥ ሆኖ አዲስ ዓመትን መቀላቀል የለባቸውም ተብሎ ስለሚታመን በሀገር ሽማግሌዎች የተጣሉትን የማስታረቅ ሥርዓትም ይከናወናል።
የመሳላ የበዓል አከባበር በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችም የሚቀጥሉ ይሆናል።
ማርታ በቀለ












Comments