top of page

ሐምሌ 8 2017 - ከኢትዮጵያ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንደኛው የአዋሽ ወልዲያ ሐራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ነው

  • sheger1021fm
  • Jul 15
  • 1 min read
ree

ባለፉት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት እና በፕሮጀክቱ ላይ ደርሷል በተባለ ጉዳት ምክንያት የፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ ኢትዮጵያን ከሶ ለረጅም ግዜ በእንግሊዝ አለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት አቁሟታል፡፡


የዚህ ፕሮጀክት ገንቢ የሆነው የቱርኩ ያፒ መርከዚ ስራ ተቋራጭ ለእንግሊዝ የህግ ባለሙያዎች ከፍተኛ ወጭ አውጥቶ ለደረሰበት ጉዳት ኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሣ እንድትከፍለው ጠይቋል።


ሆኖም ይህ ክስ በአመዛኙ ውድቅ ተደርጎበታል፡፡


ለመሆኑ በዚህ ከፍተኛ ሙግት ውጤት እንዴት ሊገኝ ቻለ?


ኢትዮጵያ ለዚህ አለም አቀፍ ሙግት እነ ማንን አቆመች?


ኢንጂነር ህሊና በላቸው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ናቸው፤ እሳቸው ለዚህ ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተውናል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ክሱ በአመዛኙ ውድቅ እንዲሆን ጥብቅ እና ከፍተኛ ጥረት እንደተደረገ ነግረውናል።


ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያቀረበውን ጥብቅ የህግ መከራከሪያና ውሎች አይቷል መባሉን ነግረውናል።


በመሆኑም ያፒ መርከዚ የስራ ተቋራጭ ይከፈለኝ ያለውን 1 ቢሊየን ዶላር የካሳ ጥያቄን ለመሞገት የኢትዮጵያ የህግ ምሁራን አሳትፈዋል ተብሏል።


ተህቦ ንጉሴ


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page