top of page

ሐምሌ 8 2017 - በአዲስ አበባ እና በሌሎችም አካባቢዎች በቀጣዮቹ 10 ቀናት የሚኖረው ከበድ ያለ የዝናብ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ተባለ

  • Jul 15, 2025
  • 1 min read

ይህንን ያለው የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት እየጣለ ያለው ዝናብ ከበድ ብሎ እንደሚቀጥል የቅድመ ትንቢያ መረጃዎች እንዳሳዩና ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡


በኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር )እንደነገሩን የክረምቱን መግባት ተከትሎ ባለፉት 10 ቀናት አዲስ አበባን ጨምሮ 70 በሚደርሱ ከተሞች ከ30 እስከ 114 ሚሊ ሜትር የደረሰ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡


በመጪዎቹ ቀናትም የዝናቡ መጠን ጠንከር እንደሚል የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ያሉን ዋና ዳይሬክተሩ በአካባቢዎቹ  ጎርፍ ሊኖር ስለሚችል በተለይ በአዲስ አበባ የውሃ ማፋሰሻ ቱቦዎች መዘጋት እንዳይኖር ለከተማ አስተዳደሩ የአደጋ ተከላካይ መስሪያ ቤት ለጥንቃቄ እንዲሆን የትንቢያ መረጃዎችን እየሰጠን ነው ብለዋል፡፡


በአብዛኛው እየጣለ ያለው የክረምቱ ዝናብ ጥሩ የሚባል ነው መሆኑን የሚያነሱት  ሃላፊው የዝናቡ መጠን በተለይ ውሃ መያዝ ላለባቸው የሃይል ማመንጫ ግድቦች የተመቸ፤ለሰብሎች እድገት ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡


እስካሁን ባለው የትንቢያ መረጃ  የአቪዬሽኑን ዘርፍ ሊያውክ የሚችል የአየር ሁኔታ የለም ሲኖር ቀድመን እናሳውቃለን ብለዋል፡፡

ከበድ ያለ ዝናብ የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ያሉ እያደጉ ያሉና የደረሱ ሰብሎች ጉዳት እንዳደርስባቸው የውሃ ማፋሰሻ ቦዮችን ከማዘጋጀት ጀምሮ በማሳዎች ላይ ጥንቃቄ ይደረግ ሲል ኢንስቲትዩቱ  መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡


ምንታምር ፀጋው

Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page