top of page

ሐምሌ 5 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም፣ ዳሽን ባንክ እና ኤታ ሶሉሽንስ የቢዝነስ ስራን የሚያቀልል የዲጅታል አገልግሎት ወደ ስራ አስገቡ።

  • sheger1021fm
  • 3 days ago
  • 2 min read

ኢትዮ ቴሌኮም፣ ዳሽን ባንክ እና ኤታ ሶሉሽንስ የቢዝነስ ስራን የሚያቀልል የዲጅታል አገልግሎት ወደ ስራ አስገቡ።


ይህ የዲጅታል መፍትሄ የወረቀት ገንዘብ ንክኪን በማስቀረት ከሀገር ሰው ጋር እና የንግድ ጠባይ ጋር ተስማምቶ የቀረበ የዲጂታል መፍትሄ መሆኑን ሰምተናል።


ይህ የዲጅታል መፍትሄ የፖስ፣ የካሽ ሬጅስተር እና የኢ.አር.ፒ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ለመስጠት የሚያስችል መፍትሄ ነው ተብሏል።


አገልግሎቱ "ዙሪያ" የተሰኘ የቢዝነስ አውቶሜሽን ሶሉሽን ሲሆን ዙሪያ ጥምጥምን መሄድ የሚያስቀር መፍትሄ መሆኑን አገልግሎት ሰጭዎቹ አስረድተዋል።


በአስመጪና ላኪ፣ በሆቴል፣ በማኑፋክቸሪንግ እና ችርቻሮ ንግድ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያዘምኑ የዲጅታል መፍትሄው ያግዛቸዋል ተብሏል።


የደንበኞችን የግብይት ተሞክሮና የአገልግሎት እርካታ በእጅጉ የሚጨምር ነው የተባለለት ይህ "ዙሪያ" የተሰኘ የኢ.አር.ፒ ፣ የፒ.ኦ.ኤስ እና ካሽ ሬጂስተር አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ለመስጠት የሚያስችል የቢዝነስ አውቶሜሽ ሶሉሽን ይፋ ተደርጎ ወደ ስራ ገብቷል።

ፈጣን የቢዝነስ ግብይት እንዲኖር፣ ግልጽ አሰራርንና ደህንነቱ የተጠበቀ ቢዝነስ እንዲቀላጠፍ ስርአቱ ያግዛል ተብሏል።


ዙሪያ የዲጅታል መፍትሄ የወረቀት ገንዘብ ንክኪን በማስቀረት ከሀገር ሰው ጋር የተስማማ የንግድ ጠባይ ጋር ተስማምቶ የቀረበ የዲጂታል መፍትሄ መሆኑን ሰምተናል።


የቢዝነስ ሶሉሽኑ ሁሉንም የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ካርዶች መቀበል የሚችል ነው ተብሏል።


በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና የተሰጠው የሂሳብ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥ እንዲሁም ነጋዴዎች የሚያንቀሳቅሱትን ሃብት በቀላሉ ለማስተዳደር እና ማንኛውንም የክፍያ መረጃዎች በአንድ ያካተተ ደረሰኝ ለማግኘት የሚያስችል ነውም ተብሏል።


"ዙሪያ" የቢዝነስ ሶሉሽንን “ኤታ” የቢዝነስ ሶሉሽን ቴክኖሎጂውን በማቅረብ፤ “ኢትዮ ቴሌኮም “ ይህንን የቴሌክላውድ መሠረተ ልማትና ከ54 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉትን የቴሌብር የክፍያ ስርዓትን በማቀበል እንዲሁም ዳሽን ባንክ ደግሞ ለአገልግሎቱ የውጪ ምንዛሪ በማቅረብ እና ከዳሸን ባንክ የክፍያ አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር አስጀምረውታል።


አገልግሎቱ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ለደንበኞች ቀላል የክፍያ አማራጭ መሆኑን ሰምተናል።


"ዙሪያ" የዲጂታል ቢዝነስ አውቶሜሽን፣ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መጫን የሚያስችል ሲሆን፣ በክላውድ የታገዘ አሰራርን አንድ ላይ አሟልቶ የያዘ ነው ተብሏል።


ነጋዴዎች፤ አገልግሎት አቅራቢዎች ከአንድ ቅርንጫፍ ምዝገባ ጀምሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።


ሶስቱ ተቋማት በሁለት ዓመታት ውስጥ ከ10,000 ለሚበልጡ ነጋዴዎች ዘመናዊ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ ስራቸው እንዲቀላጠፍ፤ የፋይናንስ አካታችነትን እንዲረጋገጥ፤ አገልግሎታቸውም የበለጠ ከፍ እንዲል በህብረት ይሰራሉ ተብሏል።


ደንበኞች ይህን አገልግሎት በ ( www.zoorya.et ) ማግኘት ትችላላችሁ ተብሏል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page