ሐምሌ 5 2017 - ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ “ንብ ተራ ኦንላይን“ የተሰኘ መተግበሪያ ወደ ስራ አስገባ።
- sheger1021fm
- Jul 12
- 1 min read
መተግበሪያው ደንበኞች ግብይቶችንና ክፍያዎችን በቀላሉ ስልካቸውን በመጠቀም ለመፈጸም የሚያስችላቸው መሆኑን ሰምተናል።
ንብ ተራ ኦንላይን በርካታ አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማከናወን የሚያስችል መተግበሪያ ነው ተብሏል።
ተቋማት የበጀት አስተዳደራቸዉን በተሻለ መንገድ እንዲመሩበት፤ ከባንክ ወደ ባንከ የሚተላለፉ ክፍያዎችን እንዲፈፅሙበት እና ሌሎች የባንከ ሥራዎችን ያቀልላቸዋል መባሉን ሰምተናል።
መተግበሪያውን ባንኩ በራሱ ልጆች እንዳበጀው ተነግሯል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ንብ ባንክ ወደ ሥራ ያስገባው ይህ መተግበሪያ ጊዜውን የዋጀ እና የባንክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለደንበኞቹ የተመቸ አገልግሎሎቶችን የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ሔኖክ ጨምረውም ይህ ሱፕርአፕ ለደንበኞች የተሟላ፤ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መተግበሪያ ነው ብለዋል።

ባንኩ አዲስ የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን ተናግሯል።
በሁሉም መመዘኛዎችም ንብ ባንክ የነበሩ ጉድለቶችን በማረም የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው ይህ ስትራቴጂ ያግዘዋል ተብሏል።
ንብ ተራ ሱፐር አፕ መተግበሪያ ለዚህ እቅድ መሳካት አንደኛው መንገድ ነው ተብሎለታል።
ይህ የ3 ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ከባንኩ ቦርድ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች ጋር ተመክሮበታል ተብሏል።
አዲሱ የንብ ባንክ ስትራቴጂ እቅድ ቀደም ሲል የነበሩ ጉድለቶችን በማረም ባንኩን ወደፊት የሚያራምዱና የሚያሳድጉ ሥራዎች እንደሚሰሩበት ተስፋ ተጥሎበታል።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments