top of page

ሐምሌ 5 2017 - በሕገ ወጥ ተግባር ላይ ተሠማርተዋል የተባሉ 6 የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች፤ ለ1 ወር ታገዱ።

  • sheger1021fm
  • Jul 12
  • 1 min read

በሕገ ወጥ ተግባር ላይ ተሠማርተዋል የተባሉ 6 የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች፤ ለ1 ወር ታገዱ።


ሌሎች ሰባት ኩባንያዎች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።


ይህን ያለው የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሲሆን የታገዱትንም ሆነ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውን የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች በስም አልጠቀሰም።


ባለስልጣን መ/ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት 6ቱ ኩባንያዎች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ ከነዳጅ አቅራቢነታቸው ለአንድ ወር እንዲታገዱ፣ 7ቱ ኩባንያዎች ደግሞ የዲጅታል ሽያጫቸው መጠን ያልተሟላ ስለሆነ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስተካክሉ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ree

በእነዚህ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ላይ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ 2.8 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ ከዲጂታል ሽያጭ ውጪ ግብይት በመፈፀማቸው ሲሆን ነዳጁን ላልተገባ ተግባር እንዲውል በማድረጋቸው እና ከሕገ-ወጥ ተግባራቸው መታረም ባለመቻላቸው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት(ዶ/ር) ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ሆነ ብለው ነዳጅ በወቅቱ ለተጠቃሚው እንዳይደርስ መንገድ ላይ ከተወሰነላቸው ጊዜ በላይ በቆሙ 253 የነዳጅ አጓጓዥ ቦቴ ባለንብረቶች ላይ ከ116 ሚሊዮን ብር በላይ መቀጣታቸውን አስታውሰዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page