top of page

ሐምሌ 4 2017 - የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል፤ ከኢትዮጵያ ብር ጋር ያለውን የምንዛሪ ተመን ይፋ አደረገ፡፡

  • sheger1021fm
  • 5 days ago
  • 1 min read

100 የኢትዮጵያ ብር በ57.5872 የሩሲያ ሩብል እንዲመነዘር ተመን ወጥቶለታል፡፡


የሁለቱ ሀገራት ገንዘቦች የእርስ በእርስ የምንዛሪ ተመን መቀመጡ በመካከላቸው ያለውን የንግድና ሌላውንም ልውውጦች በቀጥታ ለማከናወን እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡


የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ተመን ይፋ ሲያደርግ ለኢትዮጵያ ብር ኮድ 230 የመለያ ቁጥር ሰጥቷል፡፡


ከዚህ በኋላም የኢትዮጵያ ብር ከሩሲያ ሩብል ያለው የምንዛሪ ተመን በየጊዜው ማሻሻያ እየተደረገበት ይቀጥላል ተብሏል፡፡

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ከዶላር ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ ከሀገራት ጋር ያለውን የንግድና ሌላውንም ግንኙነት ለማቀላጠፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ12 ሀገራትን ገንዘብ ነው የምንዛሪ ተመን እንዲወጣላቸው ያደረገው ተብሏል፡፡


ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የተካተቱት የባንግላዴሽ፣ የባህሬን፣ የቦሊቪያ፣ የኩባ፣ የአልጀርያ፣ የኢራን፣ የማያንማር፣ የሞንጎሊያ፣ የናይጀርያ፣ የኦማን እና የሳውዲ አረቢያ ገንዘቦች መሆናቸው ተነግሯል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page