top of page

ሐምሌ 4 2017 -ብሔራዊ ባንክ፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ማዕከላዊ ግምጃ ቤትና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ለመጀመሪያ ግዜ የግምጃ ቤት ሰነዶችን ለህዝብ ይፋዊ ሽያጭ አስጀመሩ።

  • Jul 11, 2025
  • 2 min read

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ማዕከላዊ ግምጃ ቤት እና የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ለመጀመሪያ ግዜ የግምጃ ቤት ሰነዶችን ለህዝብ ይፋዊ ሽያጭ አስጀመሩ።


በዚህ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ተገኝተዋል።


እሳቸው ይህ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች የሚቀላጠፈው ገበያ የፋይናንስ አቅርቦትን ከፍ በማድረግ የተሻለ የኢንቨስትመንት አማራጭ ነው ብለዋል።


የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ነባር የመንግስት ግምጃ ሰነድ ወደ ኤሌክትሮኒክስ ተቀይረው በዚህ ገበያ መቀላጠፍ ይጀምራሉ ማለታቸውን ተናግረው መልካም የገበያ ግዜ ሲሉ አብስረዋል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው ፤ የካፒታል ገበያ በዚህ መልኩ መደራጀቱ የገንዘብ ፖሊሲ ውጤትማነትን ለማሳካት ፤ የዋጋ ግሽበትን ለማውረድ እና ብሔራዊ ባንኩ ለሚወስዳቸው አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ እርምጃዎች እንደ መሳሪያ ያገለግላል ብለዋል።

ይህ ገበያ ወደፊት እንዲመጣና ስር የሰደደ እንዲሆን በብርቱ መትጋት እንደሚያስፈልግ ማሞ ምህረቱ ጨምረው ተናግረዋል።


ይህ ገበያ የሐገር ውስጥ ካፒታልን ለማሳደግ ፤ የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳካት እና የረጅም ግዜ የኢኮኖሚ እድገትን ለመቁጠር ያግዛል ሲባል ሰምተናል።


መንግስት እዳውን እንዲያስተዳድር እና የተሻለ የፋይናንስ አማራጮች እንዲኖረው ገበያው በብርቱ እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዳይሬክተር ሐና ተልህቁ ተናግረዋል።


በኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ ስር የተደራጀው እና የመንግስት ወይም የግሉ ዘርፍ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን በአንድ ላይ ማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ የማዕከላዊ የሰነዶች ግምጃ ቤት ማደራጀት ይገኝበታል።


ይህም የሰነዶች ግምጃ ቤት የተለያዩ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ማውጣት፤ ግብይት መፈፀም እና ህጋዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ በክብር ጠብቆ የማቆየት አገልግሎቶችን በአንድ ላይ አካቶ መያዙን ሰምተናል።


በዚሁ ማስጀመርያ ላይ ኢትዮዽያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) የመንግስት የእዳ ሰነዶች በገበያው መመዝገብ በግብይት መድረኮች ላይ ለግብይት መቅረቡ ፤ ለኢትዮጵያ የእዳ ሰነዶች ገበያ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን ያስረዳል ብለዋል።


በዚህ ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ገበያ ፤ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ደላሎች የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ የውስጥ ቴክኖሎጂዎች ተዘጋጅቶ መቅረቡን ሰምተናል።


የገበያው ሥርዓት ወይም ሲስተም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማዕከላዊ የሰነድ ግምጃ ቤት ሲስተም ጋር የተገናኘ ነው ተብሏል።


ገበያው የገንዘብ ፤ የዕዳ ሰነዶች እና የአክስዮን ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ምዝገባ እና ግብይት የሚያግዝ ዘመናዊ የንግድ መድረክ አቅርቧል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page