ሐምሌ 4 2017 - በትምህርት ቤት ዙሪያ አዋኪ ድርጊት ሲፈፅሙ የተገኙ 5,220 ደንብ ተላላፊዎች ተቀጡ ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Jul 11
- 1 min read
በትምህርት ቤት ዙሪያ በ500 ሜትር ራዲየስ አዋኪ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ነበሩ ያልኳቸውን 5,220 ደንብ ተላላፊዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡
በተጨማሪም የንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተፈቀደላቸው ቦታ ውጪ #የበረንዳ_ንግድ በሚነግዱ 7,394 ደንብ ተላላፊዎች ላይም እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡
ባለስልጣኑ ይህንን ያለው በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎቹን በገመገመበት ወቅት ነው፡፡
ሌላኛው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚቆጣጠራቸው ህገ-ወጥ ተግባራት አንዱ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻን በሚመለከት መሆኑ የተነገረ ሲሆን በዚህም በበጀት ዓመቱ 12,140 ማስተካከያ ባለደረጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን መቅጣቱን ተናግሯል፡፡
በተጨማሪም የወንዝ ዳርቻ አካባቢን ባበላሹ 329 ድርጅት እና 539 ግለሰብ በድምሩ 75.7 ሚሊየን ብር ቅጣት ተሰብስቧል ያለው የባለስልጣኑ ሪፖርት እነዚህን ስራዎች ስሰራ የቆየሁት ከ27 የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ጋር ነው ብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አብሯቸው ሲሰራ ከነበሩ 27 መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ወደ 20 ዝቅ ማድረጉንም ተናግሯል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments