top of page

ሐምሌ 30 2017 - ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ህገ ወጥ እስራት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸምባቸው ኢሰመኮ አረጋግጧል

  • sheger1021fm
  • Aug 6
  • 1 min read

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ ምክንያት በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ህገ ወጥ እስራት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸምባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡


ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሰኞ ባወጣው ሪፖርት በሁለቱ ክልሎች በዳኞች እና በዐቃብያነ ሕግ ላይ ድብደባን ጨምሮ ማስፈራራት እና ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተናግሮ ይህም የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት የሚሸረሽር ስለሆነ የዳኞች ነጻነት እንዲጠበቅ አሳስቧል፡፡


በኦሮሚያ ክልል በዳኞች እና ዓቃብያነ ሕግ ላይ ለተጠርጣሪዎች ዋስትና ‹‹ፈቅዳችኋል›› ወይም እንዲፈቀድ ‹‹ተባብራችኋል›› በሚል እስራት ድብደባ እና ማዋከብ እንደሚፈጸምባቸው የተናገረው ኢሰመኮ ይህም የሰዎችን የፍትህ ተደራሽነት እንደሚሸረሽር አስረድቷል፡፡


በአማራ ክልልም በየደረጃው በሚገኙ ፍርድ ቤቶች የሚሰሩ ዳኞች ከዳኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚሰጡት ውሳኔ እና ተዕዛዝ ሳቢያ በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ሕገ ወጥ እስራት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸምባቸው ፍርድ ቤቶችም የሚሰጡትን ውሳኔ እንደማይከበር ብሔራዊው የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ተቋም ተናግሯል፡፡


ይህ በኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓት ላይ የሚያሳድረው ጫና ምንድነው? የሕገ ባለሙያዎችን ጠይቀናል፡፡


ያነጋገርናቸው በባለሞያዎች ይህን መሰል ድርጊት ለዳኞች ህገ መንግስቱ የሰጣቸውን የስራ ነፃነት መብት ከመንፈግ በተጨማሪ የሀገሪቱን የህግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page