ሐምሌ 3 2017 - አሜሪካ ለኢትዮጵያዊያን በምትሰጠው፣ የአጭር ጊዜ የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ ላይ ለውጥ አደረገች
- sheger1021fm
- Jul 10
- 1 min read
አሜሪካ ለኢትዮጵያዊያን በምትሰጠው፣ የአጭር ጊዜ የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ ላይ ለውጥ አደረገች።
እንደ ጉብኝት ላሉ ጉዳዮች የሚሰጥ የአጭር ጊዜ ቪዛ (non immigrant visa) የአገልግሎት ጊዜው ለአንድ ጊዜ ብቻ እንዲሆን መወሰኑ ተነግሯል።
የቪዛው የቆይታ ጊዜም የሶስት ወር ብቻ እንደሚሆንም አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡

እስካሁን በነበረው አሰራር ለንገድ፣ ለጉብኝት፣ ለትምህርትና ለመሳሰሉት ጉዳዮች የአሜሪካ ቪዛ የሚያገኙ ኢትዮጵያዊን የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚያበቃ ወደ አሜሪካ በተደጋጋሚ መግባት ይችሉ ነበር፡፡
የሚሰጠው የቪዛ የአገልግሎት ጊዜም ከወራት እስከ ዓመታት የሚዘልቅ ነበር።
አሁን ግን የቪዛው የቆይታ ጊዜ ሶስት ወር ብቻ ይሆናል የተባለ ሲሆን አንዴ የተሰጠ ቪዛ ከአንድ ጊዜ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመግባት አያገልግልም ሲል ኤምባሲው አስረድቷል፡፡
ከሐምሌ 1/2017 በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ግን ቀድሞ በነበረው አሰራር እንደሚቀጥሉ ተናግሯል፡፡
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments