ሐምሌ 29 2017 - ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እስላማዊ ቅርሶች እስካሁን ድረስ በተገቢው መንገድ ተደራጅተው እየተዋወቁ አይደለም ተባለ
- sheger1021fm
- Aug 5
- 1 min read
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እስላማዊ ቅርሶች እስካሁን ድረስ በተገቢው መንገድ ተደራጅተው እየተዋወቁ አይደለም ተባለ፡፡
ሀገሪቱ ውስጥ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ እስላማዊ ቅርሶች መኖራቸውን የሚጠቀስ ሲሆን ዛሬም በተገቢው መንገድ ትኩረት አላገኙም ተብሏል፡፡
የሰለብሪቲ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ካሳ ''እስላማዊ ቅርሶችና ሊጎበኙ የሚችሉ መስህቦች'' የሚል መፅሀፍን አሳትመዋል፡፡

ከአልነጃሺ መስጊድ ጀምሮ እስከ ሃረር ከተማ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ ቅርሶች መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡
ነገር ግን እነዚህ ቅርሶች ዛሬም ድረስ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ጎብኚዎች በተገቢው መንገድ እንዲተዋወቁ አልተደረገም ብለዋል፡፡
አንዳንድ ቅርሶች በዩኔስኮ መመዝገባቸውን የሚያስታውሱት አቶ አሸናፊ ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት አናሳ ነው ይላሉ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀጅ ተጓዦችን በሚያጓጉዝበት ወቅት አዲስ አበባን እንደ መተላለፊያ የሚጠቀሙ መንገደኞችን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባላቸው የሰዓታት ቆይታ ኢትዮጵያን እንዲያውቁ ተጓዦቹን ለማስጎብኘት እንደሚሞክሩ ይናገራሉ፡፡

አሁንም ድረስ ከእስላማዊ ቅርስ ጋር በተያያዘ የተደራጀ አሰራር ባለመዘርጋቱ ጎብኚዎችን በበቂ መንገድ ለማስጎብኘት እንደሚቸገሩ አቶ አሸናፊ ካሣ ያስረዳሉ፡፡
በዚህ ዘርፍ የሚታየው ክፍተት ለማስተካከል የቱሪዝሙ ቤተሰብ ፣መንግስት እና የኢትዮጵያ እስልምና እምነት አባቶች ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም ኢትዮጵያ ምን ያህል እስላማዊ ቅርስ አሏት፣ የት ይገኛሉ፣ እንዴትስ እነዚህን ቅርሶች ማስተዋወቅ ይገባል? በሚለው ዙሪያ መስራት አለባቸው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... https://www.mixcloud.com/ShegerFM/56858/
በረከት አካሉ











Choosing the Call Girl Service in Gurgaon turned out to be a great decision. The models are young, energetic, and well-groomed. They are trained to handle elite clients and create memorable experiences. Whether it’s a social event or private company, they handle everything with grace and elegance. Truly worth the price!