top of page

ሐምሌ 29 2017 -በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከአምስት ዓመት በፊት የተፈናቀሉ ሰዎች አሁንም በመጠለያ ውስጥ ናቸው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 5
  • 1 min read

በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከአምስት ዓመት በፊት የተፈናቀሉ ሰዎች አሁንም በመጠለያ ውስጥ ናቸው ተባለ፡፡


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ደቡብ ኦሞ ዞን #ዳሰነች ወረዳ በ2012 ዓ.ም በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች 79,000 እንደሚደርስ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


ኮሚሽኑ በዓመታዊ ሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው ተፈናቃዮቹ ሪፖርቱ እስከተጠቃለለበት ያለፈው ሰኔ ወር ድረስ በ12 መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡


በአፋር፣ በአማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ትግራይን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎችም የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የጠቀሰው ኢሰመኮ በቂ ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንዳልሆነ ጠቅሷል፡፡


ዘላቂ መፍትሄም ሳያገኙ ፍላጎታቸውን በበቂ ሁኔታ በሚያሟላ ሰብአዊ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ሆነው ለተራዘመ የመፈናቀል ሁኔታ ውስጥ መቆየታቸውም አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡


ኮሚሽኑ በጎርፍ የተፈናቀሉ ብሎ ከጠቀሳቸው 79 ሺህ የዳሰነች ወረዳ ተፈናቃዮች ውጭ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ቁጥርና ያሉበትን ሁኔታ ግን በዝርዝር በሪፖርቱ አልካተተም፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page