top of page

ሐምሌ 25 2017 - ''የመሬት መንሸራተት እንዳይከሰት ስራዎችን እየከወንኩ ነው'' ጎፋ ዞን

  • sheger1021fm
  • Aug 1
  • 1 min read

በጎፋ ዞን ዳግም የመሬት መንሸራተት አደጋ እንዳይከሰት ስራዎችን እየከወነ ቢሆንም የአቅም ውስንነት ግጥሞኛል ሲል የጎፋ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ።


በዞኑ የመሬት መንሸራተት አደጋ ዳግም እንዳይከሰት ለቅድመ አደጋ መከላከል ስራ መከወኛ ከተለያዩ አካላት ድጋፍን እንሻለን ብሏል።


ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በጎፋ ዞን ተከስቶ የነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ220 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል።


በርካታ መኖሪያ ቤቶችንም አወድሟል።


የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጥሪም ይህ አደጋ ዳግም እንዳይከሰት በማሰብ እንደሆነም ኮሚሽኑ ነግሮናል፡፡


ኮሚሽኑ በዚህ ክረምትም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አልፎ አልፎ የመሬት ናዳ እየተከሰተ እንደሆነም የተናገረ ሲሆን በሰዎች ላይ ግን ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳላስከተለ ሰምተናል፡፡


በዞኑ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ዳግም እንዳይከሰት በኮሚሽኑ በኩል የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎችን እና የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች እየተከወነ ነው ያሉት የጎፋ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማርቆስ መለሰ ነግረውናል።

ree

ነገር ግን አሁን እየተሰራ ያለው ስራ በበጀት እጥረት ምክንያት በቂ አይደለም ይላሉ።


ባለፈው ዓመት ተከስቶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ የአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ከእለት ድጋፍ ባለፈ በዘላቂነት የማቋቋም ስራዎች እየተከወኑ መሆኑንም አቶ ማርቆስ ነግረውናል።


በዞኑ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ቤት ንብረታቸው ከወደመባቸው መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ቤታቸው እንደተገነባላቸው እና በዘላቂነት የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንደተፈጠረላቸውም ሰምተናል።



ፍቅሩ አምባቸው

Recent Posts

See All
ታህሳስ 3/2018 የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍጆታ ካለፈው ሃምሌ ወር ወዲህ እያደገ መጥቷል ተባለ።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች ከምታመርተው የኤሌክትሪክ ሃይል 90 በመቶው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል እንደሆነ ተጠቅሷል። በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ኢትዮጵያ ከውሃ እና ከነፋስ ከ15,300 ጊጋዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨቷ ተነግሯል። በየወሩ በአማካይ 3,800 ጊጋዋት ሰአት የኤ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page