top of page

ሐምሌ 23 2017 - የምክክር ኮሚሽንን ተልዕኮና ዓላማ ተረድተው አብረውት እየሰሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥቂቶች ብቻ ናቸው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jul 30
  • 1 min read

በኢትዮጵያ ካሉ ወደ 5,000 ገደማ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ተልዕኮና ዓላማ ተረድተው አብረውት እየሰሩ ያሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው ተባለ፡፡


ይህን ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ነው፡፡


ምክር ቤቱም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የኮሚሽኑን ዓላማ ካለመረዳትና በፋይናንስ እጥረት ምክንያት በሚፈለገው ልክ በአገራዊ ምክክሩ ላይ እየተሳተፉ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡


በምክሩ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚፈለገው ደረጃ በንቃት አለመሳተፍ እንደሚያሳስበው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተናግሯል፡፡


ድርጅቶቹ በምክሩ ላይ እንዲሳተፉ ማህበረሰቡንም እንዲያነቁ አለም የገንዘብ ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ እንዳልሆነ ምክር ቤቱ ጠቁሟል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page