ሐምሌ 22 2017 - የውጭ ምንዛሪ በገበያው እንዲወሰን ያስቻለ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ከተደረገ ዓመት ሆነው፡፡
- sheger1021fm
- Jul 29
- 1 min read
ሪፎርሙ የብሔራዊ ባንክ የመጠባበቂያ ክምችትን ማሳደጉ፣ በወጪ ንግድ በመሳሰሉት ከፍተኛ ውጤት እንዲመጣ ማስቻሉ ተነግሯል፡፡
ለንግድ፣ ለትምህርት፣ ለጉብኝት ወደ ውጪ ሀገር የሚሄዱ ሰዎችም ማሻሻያው ከተደረገ በኋላ በተሻለ መጠን ዶላር እየቀረበላቸው መሆኑም ይሰማል፡፡፡
ግን ባንኮች ዶላር ለጠየቃቸው እስከ 200 በመቶ ተቀማጭ እየጠየቁ ነው የሚል ክስ ቀርቧል፡፡
ማዕከላዊ ባንኩ በቂ የውጪ ምንዛሪ እና መደላድል አለ ቢልም ባንኮች ግን በምትኩ የውጭ ምንዛሪ ለመስጠት እስከ 200% ተቀማጭ እየጠየቁ ነው ፤ ቢውሮክራሲም እያበዙ ነው ተብሏል።
ብሔራዊ ባንክም ይህንን የሚያደርጉትን ጠቁሙኝ ብሏል፡፡ ባለሞያዎችስ ምን ይላሉ?
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments