ሐምሌ 21 2017 - ዶ/ር አብዱ አደም የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ተሹመዋል
- sheger1021fm
- Jul 28
- 1 min read
ኢትዮጵያዊው ከፍተኛ የካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም፤ የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው መሾማቸው ተነገረ።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የካንሰር ህክምና ክፍል ከፍተኛ የካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር አብዱ አደም የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ ( #ASCO ) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው ተሹመዋል።
በዚህም ዶ/ር አብዱ ከሌሎች የምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የካንሰር ክብካቤ እና ህክምና (ኦንኮሎጂ) ባለሙያዎችን ይደግፋሉ ተብሏል።

የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) በካንሰር መከላከል ላይ የሚከውናቸውን ስራዎች እንዲሁም በካውንስሉ ውስጥ ስለተሰጣቸው ኃላፊነት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር አብዱ አደም ጠይቀናል፡፡
ኃላፊነቱ ኢትዮጵያ #ካንሰርን ለመከላከል የምትከውናቸው ስራዎች እንደሚያግዝ ነግረውናል፡፡
በተጨማሪም ካንሰር ላይ የሚደረጉ ምርምሮች እንዲሁም የባለሙያዎች ስልጠና በካውንስኑ እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡
የአሜሪካ ክሊኒካል ኦንኮሎጂ (ASCO) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክልላዊ ምክር ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ የካንሰር መከላከል ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ሲደግፍ እንደነበር የሚጠቅሱት ዶ/ር አብዱ አሁንም የተሰጠው ኃላፊነት ይበልጥ የሚጠቅም ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር አብዱ አደም የካንሰር ሕክምናን በኢትዮጵያ እንዲሁም በቀጠናውና ከዚያም በላይ ለማሳደግ ለሚከውኑት ስራ እንዲሁም ለካንሰር ህክምና አገልግሎትና ለህክምና ትምህርት ክፍሉ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፆ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ዕውቅና እንደተሰጣቸውና በሚያዝያ ወር ልዩ ሽልማት ማበርከቱን ሰምተናል፡፡
ሙሉበ ዘገባውን ያድምጡ……
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments